የምግብ ስርዓትን ለማሻሻል የጥናትና ምርምር ሥራን በማጠናከር ለተለያዩ ውሳኔዎች በር እንዲከፍቱ ማስቻል ላይ ሊሰራ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ ተናገሩ
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከተለያዩ ዞኖችና ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ የሥነ-ምግብ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች ለ4 ቀን የቆየ ሰልጠና ሰጥቷል።
በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብሔራዊ የሥነ-ምግብ መረጃ ማዕከል አሰተባባሪ ዶ/ር አረጋሽ ሳሙኤል በንግግራቸው፤ የስልጠናው ዓላማ በየክልሉ ያሉ የጤና ኢንስቲትዩቶችን ማጠናከርና ከሥርዓተ ምግብ አንፃር በክልሉ ያሉ ባህላዊ ምግቦችን በመጠቀም የምግብ ደህንነትን ለማረጋገጥ ግንዛቤ አግኝተው እንዲያሰተዋውቁና የመረጃ ልውውጥ ሥርዓትን በማጠናከር ለውሳኔ ሰጪ አካላት ምቹ ማድረግ ላይ ያተኮረ ስልጠና መሆኑን አንስተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አጉኔ አሾሌ በበኩላቸው፤ በሥርዓተ ምግብ ዙሪያ የሚደረጉ ጥናቶች ምርምሮች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል በመሆኑ ስልጠናውን የሰጡ አካላትን አመስግነዋል።
እንደ ሀገር የመቀንጨር አደጋ 41 በመቶ ነው ያሉት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ፤ ሰልጣኞቹ ባገኙት ግንዛቤ ከሥርዓተ ምግብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በተጨባጭ መረጃ በመያዝ በጥናትና ምርምር በማሻሻል ለተለያዩ ውሳኔዎች በር እንዲከፍቱ ማስቻል ላይ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ለዚህም ተቋሙ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እንደሚያግዝ አመላክተዋል።
ከሰልጣኞች መካከል አንዳንዶች በሰጡት አሰተያየት በጥናት የተመሰረተ የመረጃ አያያዝ ሥርዓትን በመዘርጋት ትክክለኛ መረጃ በማውጣት ለጥናትና ለፖሊስ አውጪዎች ምቹ ሁኔታ መፍጠር የሚያስችል ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ