የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2017 ዓ.ም የ6 ወር አጠቃላይ አፈፃፀሙን በጂንካ ከተማ ገምግሟል
ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በትምህርቱ ዘርፍ ለማረጋገጥ የሴቶች ተሳትፎን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ ገልፀዋል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች የተከናወኑ የተጠቃለለ የትምህርት ሥራ ዕቅድ አፈፃፀም የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በጥልቀት ገምግሟል።
መድረኩን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ እና የቢሮው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደፋሩ በጋራ መርተውታል ።
የቢሮዋ ኃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ በአፈፃፀም ግምገማው ወቅት እንደገለፁት የትምህርት ስብራትን ለመጠገንና ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉ አቀፍ ለውጥ በዘርፉ እንዲመዘገብ የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ አንስተዋል።
በአፈጻጸም ወቅት በድክመት የተነሱ ተግባራትን በማረም ጥንካሬችን በማስቀጠል ተማሪውን ውጤት ለማሻሻል ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመርሃ ግብሩ የሴክተሩ የ2017 ዓ.ም የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ በምክትል ቢሮ ኃላፊና አስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምሩ ቡራይና የመጀመሪያ ሰነድ የቀረበ ሲሆን አለም አቀፍ ሴቶች ቀንን አስመልክቶ በስርዓተ ፆታ ክፍል ተወካይ ወይዘሮ ተስፋነሽ ግርማ አማካይነት ሰነድ ቀርቦ በተሳታፍው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/