ሴቶችን በልማት ሕብረት በማደረጀት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት አበርታች ውጤት መመዝገቡ ተገለጸ

ሴቶችን በልማት ሕብረት በማደረጀት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት አበርታች ውጤት መመዝገቡ ተገለጸ

የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በልማት ህብረት የተደራጁ ሞዴል ሴቶችን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የሴት አመራሮች በአካባቢው ተዘዋውረው የመስክ ምልከታ በማድረግ እለቱን በድምቀት አክብረዋል።

የክልሉ ከፍተኛ የሴት አመራሮች ቡድን በይርጋጨፌ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌያት በመዘዋወር በሴቶች ልማት ሕብረት የተሠሩ የሌማት ትሩፋት፣ በግብርና፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ ዘርፎችና በበጎ ፈቃድ ሥራ የተከናወኑ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ተንቀሳቅሰው ጎብኝተዋል።

የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል እና የፋይናንሰ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም ከበደ በአለም አቀፍ ደረጃ 114ኛ ጊዜ በሀገር ደረጃ ለ49ኛ ጊዜ የሚከበረዉን ማርች 8 በዓል ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ቀበሌያት በሴቶች በልማት ቡድን እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

በወረዳው የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን መስክ ምልከታ ከማድረግ ባለፈ ለተጠቃሚነታቸው አስፈላጊ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በዓሉን ማክበር እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

በሀገር ደረጃ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉ አቀፍ ለውጥ በሴቶች ይረጋገጣል” ሚል መሪ ቃል በዓሉ እንደሚከበር ጠቁመው፥ ሴቶች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚነታቸው ላይ የታዩ ለውጦችን በማጠናከር ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሠራ ይገባልም ብለዋል።

በተለይም ቡድኑ ባደረገው የመስክ ምልከታ ሴቷ በልማቱ ከተሳታፊነትና ከተጠቃሚነት አንፃር የተጀመሩ ሥራዎች ቢኖርም በቀጣይ ለሴቶችን ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በኢኮኖሚው ዘርፍ በቅንጅት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

የክልሉ ኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ምክትል ስራ አሰኪያጅ ወ/ሮ ድንቅነሽ በራቆ እንደተናገሩት፣ ሴቶች በኢኮኖሚው ዘርፍ ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥ አኳያ የታዩ ለውጦቾ አበረታች ቢሆንም በቀጣይም እርስ በእርስ በመደጋገፍ፣ ቁጠባን ባህል በማድረግና፣ የኑሮ ውድነትን ጫና በመቀነስ፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ገቢያቸውን ከማሳደግ አኳያ በትኩረት መሠራት አለበት በማለት አመላክተዋል።

ጉብኝቱ ተሳታፊዎች በሴቶች ልማት ህብረትየተከናወኑ ተግባራት የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችል ሥራዎች መከናወኑን ጠቅሰው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግ የኢዲዶ፣ የሀሩና የጭቶ ቀበሌያት ሞዴል የሴቶች ልማት ህብረት የተደራጅ ማህበራት የመስክ ምልከታ የተደረገ ሲሆን ሴቶቹ በልማት ቡድን ተደራጅተው በመስራታቸው ኢኮኖሚያቸውንና ኑሮአቸውን ማሻሻል መቻላቸውን አንስተው በግብርና፣ በቡና ችግኝ በማዘጋጀት፣ ከብቶች በማደለብ፣ በቃጫ ንግድ፣ በዶሮ እርባታ፣ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሴቶቹ በቀጣይ ኢኮኖሚያቸውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቋል፡፡

ዘጋቢ፡ ጽጌ ደምሴ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን