በተለያዩ ዘርፎች ህብረተሰቡን በማሳተፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ውጤት እያመጡ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አዝመራዉ አንደሞ
ሀዋሳ፡ የካቲት 26/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የህዝብ ተመራጭ የሆኑ የክልል እና የፌዴራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ቀጣይ የልማት ስራዎች እና የትኩረት አቅጣጫዎች ዙርያ ከአስፈፃሚ አካላት ጋር በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ውይይት አካሂደዋል ።
በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አዝመራዉ አንደሞ እንደገለፁት በመንግሥት የተጀመሩ የተለያዩ የልማት ኢንሼቲቮች በክልሉ ተግባራዊ ማድረግ ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደምገባ ተናግረዋል ።
በአካባቢው የሚገኙ የተፈጥሮ ፀጋዎችን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የልማት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልፀው በግብርናው ዘርፍ የእንሰት ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች እንደሆነ ገልፀዋል ።
በክልሉና በፌደራል መንግሥት የተጀመሩ የመንገድ መሠረተ ልማቶች ተፈፃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የክትትል ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ አንስተው ሁሉም ዘርፉን እንዲደግፍ አሳስበዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ትምህር ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በበኩላቸው የአካባቢው ማህበረሰብ የልማት ስራዎች ላይ እያደረጉት ያለው ተሳትፎ የሚመሰገን እንደሆነ አንስተው ይህ መልካም ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል ።
ችግሮች ደረጃ በደረጃ እንዲፈቱ ለማድረግ የህዝብ ውይይቶች አስፈላጊ መሆናቸውን ገልፀው ለዚህም ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
የክልሉን ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎችን ለመፍታት የአመለካከት ለውጥ በማድረግ ተቀናጅቶ በመስራት የተጀመሩ መሠረተ ልማት ስራዎችን ማስቀጠል ያሰፈልጋል ብለዋል።
በዚህ ውይይት ላይ የተሳተፉ አስፈፃሚ አካላትም የዞኑን ሰላም ማስቀጠል ለልማት መሠረት በመሆኑ ህገ ወጥነትን በመከላከል በኩልም ትኩረት መደረግ እንዳለበት ተናግረው የመንገድ መሠረተ ልማት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች መቅረፍ በክልሉና ፌዴራል መንግሥት ትኩረት ሊደረግ እንደምገባ አንስተዋል ።
በመድረኩም ላይ የህዝብ ተመራጭ የሆኑት የዞን፣ የክልል እና የፌዴራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የዞን የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች ተሳትፈዋል ።
ዘጋቢ፡ አስቻለው አየለ- ከማሻ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/