በመጪው በልግ 81 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት ከ2.8 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ ጥሎ ወደ ስራ መግባቱን የደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ
ሀዋሳ፡ የካቲት 26/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በመጪው በልግ 81 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት ከ2.8 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ ጥሎ ወደ ስራ መግባቱን የደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል፡፡
የ2017 በልግ አዝመራ ተግባራት “የግብርና ምርታማነት ብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል የማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ በደቡብ ኦሞ ዞን ተካሂዷል።
የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ምንላርገው አዲሱ ባደረጉት ንግግር፤ መንግስት የህብረተሰቡን የኢኮኖሚ ለውጥ በማምጣት ከተረጅነት በዘላቂነት ለማላቀቅ እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
እንደ መምሪያ ኃላፊው ንግግር በ2016 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ሰብሎች 73 ሺህ 7 መቶ 25 ሄክታር በማልማት ከ3 ሚሊየን 772 ሺህ 4 መቶ 41 ኩንታል ምርት ለማግኘት ከተጣለው ግብ 77 ሺህ 1 መቶ 88 ሄክታር በላይ በማልማት 2 ሚልየን በላይ ኩንታል ምርት ተገኝቷል ብለዋል።
በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ረገድ አጥጋቢ እንዳልነበር ጠቁመው በቀጣይ ትልቅ ትርጉም ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማልኮ በንቅናቄ መድረኩ ባደረጉት ንግግር፤ እንደ ዞን አርሶና አርብቶ አደር ማህበረሰቡ ራሱ ከተረጅነት ተላቆ በሁሉም መስክ ለውጥ በማምጣት ራሱን እንዲችል እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የተስተዋሉ ማነቆዎችን በመፍታት በተለይም የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ሀገራዊ ብሎም አካባቢያዊ የምርት እጥረትን በመሻገር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መስራት ወሳኝ መድረክ ነው ብለዋል።
መድረኩን በይፋ የከፈቱት የድቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ ዶክተር ኦላዶ ኦሎ እንዳሉት፤ መንግሥት ብልጽግናን ለማረጋገጥ ግብርናን ማዘመን ላይ ትኩረት ሰጥቶ እተየሰራ ነው።
የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ በመስኖ ስራን ይበልጥ ማጎልበት፣ የግብርና መካናይዜሽን ላይ በማትኮር ለኢንዱስትሪና ወጭ ንግድ በቂ ምርት የማቅረብ፣ ለአየር ለውጥ የማይበገር የግብርና ስራ በማጠናከር የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት መሰራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
ከመንግስት ጋር በቅርበት በመስራት የማህበረሰቡን አስተሳሰብ በመቀየር የተለያዩ እገዛ እያደረገ የሚገኘው የኃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን ምክትል ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሶስና ኃይለማርያም ንቅናቄ መድረኩ ላይ ተኝተው ባስተላለፉት መልእክት፤ ዞኑ ከፍተኛ እምቅ ሀብት ቢኖረውም በርካታ ማነቆዎችና ውስንነት በመኖሩ ከአቅም በታች በመሰራቱ የምግብ እጥረት እና ስነ-ምግብ ክፍተት ውስጥ እንደሚገኝ እንስተዋል፡፡
እነዚህ ውስንነቶችን በመፍታት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በግብዓት አቅርቦት በክህሎት ዙሪያ ስልጠና በመስጠት ረገድ ፕሮጀክቱ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
መንግሥት ብልጽግናን ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አርብቶ አደሮች በምርታማነት ላይ በማትኮር ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች እንዲያቀርብና በሰላም ዙሪያ ያለውን በተለይም በድንበር አካባቢ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አሁንም በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ጳውሎስ አሚገሮ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/