የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የሴቶች ሚና በሚል የውይይት መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው
በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ስራ አስፈፃሚ እና የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ሀላፊ እሌኒ አባይነህ፤ ፓርቲው ባካሄዳቸው መደበኛ ጉባኤዎች ላይ ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች የህዝቡን ሰላምና ልማት በዘላቂነት እንዲረጋገጥ ሴቶች በግንባር ቀደምነት ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
ሴቶች በልማት ብቻ ሳይሆን በጦር ሜዳ ላይ ለተቀዳጁት ድል አድዋ ማሳያ ነው የሚሉት ወ/ሮ እሌኒ፤ ሴቶች በሰላሙ ዘርፍም የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ አይተኬ ነው ብለዋል።
የጋሞ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሀኪሜ አየለ በበኩላቸው፤ በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች መተላለፋቸውን ገልፀው ብልፅግና ፓርቲ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል በማለት ተናግረዋል።
የጋሞ ዞን ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ደመረ፤ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካውና በመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሴቶች እንዲሳተፉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በአደረጃጀት እንዲታቀፉ ፓርቲው በርካታ ስራዎችን እየሰራ ነው ብለዋል።
በመድረኩ በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች እየቀረቡ ሲሆን በቀጣይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
በመድረኩ የክልል እና የዞን የፓርቲ ስራ አስፈፃሚዎችን ጨምሮ ከዞንና ከከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የሴቶች ክንፍ አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ: ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/