የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ እያካሄደ ነው

የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ እያካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ የካቲት 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃ ግብር 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

የጎፋ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወ/ሮ አበበች መርጊያ ጉባኤውን ሲከፍቱ እንዳሉት ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት እና የዴሞክራሲ ስርዓት መገለጫ በመሆናቸው አስፈፃሚ መስራያ ቤቶችን በመከታተል፣ በመደገፍ፣ በመገምገም እና ቅንጅታዊ አስራሮችን በማጠናከር ህብረተሰቡ ፍትሐዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ለተግባሩ መሳካት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

የጉባኤው አባላት የሀገሪቱና የአከባቢዉን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን በመረዳት የተሰጣቸዉን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የምክር ቤት አባላት በቀረቡ አጀንዳዎች ዙሪያ በጥልቀት በመወያየት የተጣለባቸውን የህዝብ ውክልና ስራ በአግባቡ እንዲወጡ ምክትል አፈ ጉባኤዋ አሳስበዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊበ አየለ የዞኑን የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤት አቅርበዋል።

አስተዳዳሪው በግማሽ ዓመቱ በዞኑ በአዝርዕትና በሆርቲካልቸር ሰብሎች ከ67 ሺህ ሄክታር በላይ ለማልማት ታቅዶ ከ66 ሺህ ሄክታር በላይ ማልማት መቻሉን ገልጸዋል።

ከ12 ሺህ በላይ ወጣቶችን በሶስቱ ዕድገት ተኮር ዘርፎች በከተማና በገጠር ወደ ስራ ማስገባት ስለመቻሉ አስተዳዳሪው በሪፖርታቸው አንስተዋል።

በገቢ ስራዎች አፈፃፀም ባለፉት ስድስት ወራት ከ740 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ601 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡ ተገልጿል።

ለምክር ቤቱ በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ በምክር ቤት አባላት ውይይት ተደርጎበት እንደሚጸድቅ እና ተጨማሪ በጀትና የተለያዩ ሹመቶችም ቀርበው እንደሚያጸድቁ ይጠበቃል።

በጉባኤው የዞንና የክልል ምክር ቤት አባላትና ተጋባዥ እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን