የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ

የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ

ሀዋሳ፡ የካቲት 23/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በየካቲት ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች በነዳጅ ውጤቶች ግብይት አዋጁና በአሠራር መመሪያው መሠረት መንግስታዊ ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጥብቅ አሳስቧል፡፡