የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች 129ኛውን የዓድዋ ድል በዓል አስመልክተው ለኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የዓድዋ ድል አንድነት እና ብሔራዊ ኩራትን የሚገልጽ ነው ብሏል።
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ባስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለኢትዮጵያ ብልጽግና እና ስኬትን ተመኝቷል።
በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ባስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፣ ሁለቱ ሀገራት በታሪክ ጀግንነትን፣ አንድነትን እና ጽናትን የሚጋሩ መሆናቸውን ጠቅሷል።
ሀገራቱ ከታሪኮቻቸው ባሻገር መጪዎቹ ጊዜያት ብሩህ እንደሚሆኑም እምነቱን ገልጿል።
በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያዊያን የጽናት እና የአንድነት ምልክት መሆኑን በመግለጽ፣ ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የእንግሊዝ፣ የጀርመን እና የኩባን ጨምሮ የተለያዩ ኤምባሲዎች ለበዓሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል በሀገር ውስጥ እና በተለያዩ የዓለም ሀገራት በሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

More Stories
የቡርጂ ዞን ምክር ቤት አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ ወጌ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ
የወባ በሽታ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠርን ጉዳይ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ