ሀዋሳ፣ የካቲት 21/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ ) አካደሚው ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ እና ሴቶች ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር “ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለእምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል ከክልል ከዞንና ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ሴቶች በሳጃ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ምክትል እና የስልጠና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልበር ኡስማን እንዳሉት አካዳሚው በክልሉ ሴቶችን በማብቃት ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነታቸውን ለማጎልበት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ላይ ይገኛል ።
ተቋሙ ከቀበሌ ጀምሮ በየመዋቅሩ የሚያደርጋቸው የስልጠና ዳሰሳ ጥናትና የተቋማት ፍላጎት መነሻ አድርጎ ሴቶችን በማብቃት የመሪነት ክህሎታቸውን ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በማከናወን ላይ ነው ብለዋል አቶ አብዱልበር።
ውስን የማህበረሰብ ክፍሎች በማሳተፍ የሚፈለገውን ውጤት ማሳካት አዳጋች ነው ያሉት ምክትል ሀላፊው በመሠረታዊ የመሪነት ጥበብ እና ሴቶችን ማብቃት እንዲሁም የስርዓተ ፆታ አካቶ ትግበራ ቁልፍ ተግባራት በመሆናቸው ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል ።
የክልሉ ሴቶች እና ህፃናት ቢሮ ምክትል እና የሴቶች ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ነጅሚያ ራህመቶ በበኩላቸው ስልጠናው በክልሉ የሚገኙ ሴቶች አቅም በመገንባት በኢኮኖሚ በፖለቲካ እና በማህበራዊ ዘርፎች እኩል ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።
ከክልል ከዞንና ልዩ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ በአፈፃፀማቸው ግንባር ቀደም አንድ መቶ ሴቶች ስልጠናውን መውሰዳቸውን የገለፁት ምክትል የቢሮ ሀላፊዋ ለመሰል ስራዎች ከአካዳሚው ጋር ተቀናጅተው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል ።
ስልጠናው የሴቶችን ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማሳደግ አጋዥ እንደሆነ አመላክተው ሰልጣኞቹ ለተግባራዊነቱ ተግተው እንዲሰሩም አስገንዝበዋል ።
ሰልጠኞቹ በሰጡት አስተያየት በስልጠናው በተሰማሩበት የስራ መስክ ተግባራትን በውጤታማነት በመፈፀም ግንባር ቀደም መሆን የሚያስችል ግንዛቤ እንደጨበጡበት ተናግረዋል ።
አክለውም ያገኙትን እውቀት በየሴክተሮቻቸው ለሚገኙ ሴቶች እና ባለድርሻ አካላት በማጋራት ወደተግባር ለመቀየር ጥረት እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል ።
ዘጋቢ ፦ሪድዋን ሰፋ ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሳውላ ካምፓስ ለ9ኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 121 ተማሪዎችን አስመረቀ
ዲግሪው “ወረቀት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ተስፋና የትውልድ ኃላፊነት ነው” – አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር)
በክልሉ የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ገለጹ