የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ከክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር ከክልሉ ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ሴቶች ስልጠና መስጠት ጀመረ

ሀዋሳ፡ የካቲት 19/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ከክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር “የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለእምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል ከክልሉ ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ሴቶች በሳጃ ከተማ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ፤ ለሰልጣኞች ባስተላለፋት መልዕክት እንዳሉት፤ አካዳሚው በዋናነት በክልሉ በአመራር ደረጃ ላይ የሚገኙ ፈፃሚዎችን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች አጫጭር እና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም በክልሉ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎች በመስራት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተከታታይነት ያላቸው ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል።

የክልሉ ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሀመድናስር በበኩላቸው፤ የሴቶችን ተሳትፎ ተጠቃሚነት እና ውሳኔ ሰጪነት በማጎልበት በሀገሪቱ በሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ እምርታ ለማምጣት የሴቶችን አቅም መገንባት ፋይዳው ሁለንተናዊ ነው ብለዋል።

ስልጠናው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱን ጨምሮ የክልሉ ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ዘቢባ አብድልናስር፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ሺመልስ፣ የአመራር አካዳሚዉ ምክትል ዳይሬክተር እና የስልጠና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልበር ኡስማን እና ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተጀምሯል።

ስልጠናው በመሠረታዊ የመሪነት ጥበብ እና ሴቶችን ማብቃት እንዲሁም በስርዓተ ፆታ አካቶ እና በሴቶች ማብቃት ዙሪያ ለተከታታይ ሦስት ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ዘጋቢ፡ ሪድዋን ሰፋ – ከወልቂጤ ጣቢያችን