ምክር ቤቱ ታች ድረስ በመውረድ የክትትልና ቁጥጥር ስራ በመስራቱ የውሸት ሪፖርት መጠን በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ገለፀ
”አፊኒ” ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትን ከመደበኛ የፍትህ ተቋማት ጋር በቅንጅት የፍትህና እርቅ አገልግሎት እንዲሰጥ አዋጅ መዘጋጀቱም ተመልክቷል።
የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ፤ በበጀት አመቱ ምክር ቤቱ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን የዕቅድ ክንውን በጥብቅ እየተከታተለ ስለመሆኑ በማንሳት ግድፈቶች እንዲታረሙ እያደረገም ነው ብለዋል።
ከፅሁፍ ሪፖርቶች ይልቅ ተግባራትን ወረዳና ቀበሌ ድረስ በመውረድ እተመለከተ በመሆኑ የውሸት ሪፖርት መጠንን ዝቅ ማድረግ መቻሉን አረጋግጠዋል።
በአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች መካከል የስራ ፉክክር መንፈስ ለመፍጠር የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ መስሪያ ቤቶች ይሸለማሉ ብለዋል።
ህብረተሰቡን በሚገባው ልክ ተጠቃሚ ያላደረጉና ሀላፊነታቸውን ባልተገባ መልኩ የተጠቀሙ አመራሮች ላይ እርምጃ የክልሉ መንግሥት መውሰዱንም አፈ ጉባኤዋ አስረድተዋል።
ዘጋቢ: ጀማል የሱፍ

More Stories
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን አካሂዷል
በከተማ እና በገጠር ልማት መካከል ያለውን ትስስር ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ