በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የህዝቡን የልማት ፍላጎት በሚመጥን መልኩ ምላሽ ለመስጠት አመራሩ በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበት የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት አሳሰበ
ሀዋሳ፡ የካቲት 19/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የህዝቡን የልማት ፍላጎት በሚመጥን መልኩ ምላሽ ለመስጠት አመራሩ በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበት የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት አሳስቧል፡፡
የዞኑ ምክር ቤት አባላት በተለያየ ጊዜ የሚሰይማቸው አመራሮች የማስፈፀም አቅማቸውን ይበልጥ በማሳደግ በአገልጋይነት መንፈስ በቁርጠኝነት ህዝቡን ማገልገል እንዳለባቸው ነው 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉበኤውን ባካሄደበት ወቅት ያሳሰበው።
ልማታዊ ሥራዎች በአግባቡ ተፈፃሚ እንዲሆኑ አስፈፃሚ አካላትን በመደገፍና ግንባር ቀደም ሚናቸውን እንደሚወጡም የምክር ቤቱ አባላት አረጋግጠዋል።
የ2017 ዓ.ም ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ምክር ቤቱ አዳምጦ በጉድለት የተመዘገቡ እንዲታረሙ የተሰጡ የልማት ክፍተቶችን አስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶችን በማቀናጀት ለተሻለ ውጤት እንደሚሠራ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ገልፀዋል።
የዞኑ የመምሪያ ሀላፊዎችም የበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በምክር ቤት አባላት ክፍተት ተብለው የተለዩትን የቀጣይ የዕቅድ አካል አድርገው እንደሚሠሩ ገልጸዋል።
በጉባኤው የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ በጉባኤ በዋና አስተዳዳሪ አቅራቢነት ቀርቦ የምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
በተመሳሳይ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቅራቢነት የቀድሞ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንዲነሱ ለምክር ቤት አባላት ቀርቦ አስተያየት ከተሰጠ በኋላ በአራት ድምፅ ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን በምትካቸው አዲስ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በዕጩነት ቀርበው የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ ይሁንታ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ዋና አስተዳዳሪው የአምስት የመምሪያ ሀላፊ አመራሮች አዲስ ሹመትና የስድስት መመሪያ ሀላፊዎች ሽግሽግ የተደረገባቸው ለምክር ቤት አባላት አቅርቀው በምክር ቤት አባላት ሙሉ ይሁንታ ተሰጥቷል።
የዞኑ ምክር ቤት የህግ ፍትህ መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዕጩ በደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ በኩል አቶ ኦሉሉ ቻርነል ቀርበው በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሎስንዴ ሎኛሱዋ በበኩላቸው፤ አመራሩ በጊዜ የለሽ መንፈስ ህዝቡን ማገልገል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አዲስ የተሰየሙ ተሿሚዎች በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችኝ
More Stories
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ከክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር ከክልሉ ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ሴቶች ስልጠና መስጠት ጀመረ
ምክር ቤቱ ታች ድረስ በመውረድ የክትትልና ቁጥጥር ስራ በመስራቱ የውሸት ሪፖርት መጠን በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ገለፀ
በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዕውቀት የተካነ እና ሥራ ፈጣሪ ዜጋን ለመፍጠር በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ