በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዕውቀት የተካነ እና ሥራ ፈጣሪ ዜጋን ለመፍጠር በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሣይንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 ዓ.ም የ6 ወራት ክንውን አፈጻጸም ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ እያካሔደ ነው።
የቢሮው ሀላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት፤ በሣይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎት የበቃ ህብረተሰብ ለመፈጠር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ቢሮው በክልሉ ያሉ ዞኖችና የክልል ማዕከላትን በቴክኖሎጂ ለማስተሣሰር እና የኮደርስ ስልጠናም በትኩረት እየሠራ ስለመሆኑ አቶ ተካለኝ አስረድተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ምክር ቤት ሴቶች ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እመቤት ወንድሙ በበኩላቸው፤ ዓለም በዲጂታል ቴክኖሎጂ የደረሰበትን ደረጃ ለመቀላቀል በፈጠራ የተካነ ዜጋ በመፈጠር ድህነትንና ኋላ ቀርነትን ለመቅረፍ ሁሉም በትኩረት መሥራት እንዳለበት ተናግረዋል።
በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ተነሳሽነት የተጀመረውን የኮደርስ ስልጠና የክልሉ ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑም ቢሮው የተጣለበትን ሀላፊነት በትኩረት እንዲወጣ ወ/ሮ እመቤት አስገንዝበዋል።
ቢሮው የ2017 ዓ.ም የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በኮንሶ ዞን በመገምገም ላይ ነው።
ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን አካሂዷል
በከተማ እና በገጠር ልማት መካከል ያለውን ትስስር ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ