የክልሉ ምክር ቤት ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እየሰራ ነው – ዋና አፈ ጉባኤ ፋንታዬ ከበደ
ሀዋሳ፡ የካቲት 19/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የክልሉ ምክር ቤት ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እየሰራ መሆኑን የሲዳማ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንታዬ ከበደ ገለጹ፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው።
በምክር ቤቱ ጉባኤ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ እንደገለፁት፤ ምክር ቤቱ ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እየሰራ ነው።
ምክር ቤት በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ ሁለንተናዊ እንቅሰቃሴዎችን የቅርብ ክትትል እያደረገ ነው ብለዋል።
ምክር ቤቱ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ግብረ መልስና አቅጣጫ እየሰጠ ስለመሆኑም አፈ ጉባኤዋ ተናግረዋል።
ከዛሬ ጀምሮ በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤው የባላፈውን ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፣ የበጀት አመቱን የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን የግማሽ አመት አፈፃፀም በዝርዝር መገምገም። የገቢ ዕቅድ መከለስ፣ የክልሉን ተጨማሪ በጀት ማፅደቅ፣ አዋጆችንና ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/