የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉበኤ በዲመካ ከተማ ማካሄድ ጀመረ

የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉበኤ በዲመካ ከተማ ማካሄድ ጀመረ

ሀዋሳ፡ የካቲት 18/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ፣ 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉበኤ በዲመካ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አፈጉባኤ አቶ ሎስንዴ ሎኛሱዋ እንደገለፁት፥ የዞኑ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ተረጋግጦ ፖለቲካዊ መስተጋብራቸው ከፍ እንዲል የምክር ቤት ከባላት ጠንክረው መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በዚህም የአስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች የሥራ ሪፖርታቸውን በመከታተል፣ ቁጥጥር በማድረግና ድጋፍ በመስጠት የተጣለባቸውን የህዝብ አደራ መወጣት እንዳለባቸውም አቶ ሎስንዴ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክር ቤቱ የደቡብ ኦሞ ዞን ሽግግር ም/ቤት 4ኛ ዙር፣ 11ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ረቂቅ ቃለ ጉባኤ መምርምሮ ማጽደቅ፣ የዞኑ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት መርምሮ ማጽደቅ እና ስንብትና ሹመት ላይ በዝርዝር ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጀንካ ጣቢያችን