“የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የግብርናው ዘርፍ ተመራማሪዎች ድርሻ ላቅ ያለ ነው” – ኡስማን ሱሩር
ሀዋሳ፡ የካቲት 18/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የግብርናው ዘርፍ ተመራማሪዎች ድርሻ ላቅ ያለ ነው ሲሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ኡስማን ሱሩር ገለጹ፡፡
የክልሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አመታዊ ጉባኤ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ኡስማን ሱሩር፤ የግብርና ተመራማሪዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማፍለቅ ሃላፊነት አለባቸው ነው ያሉት።
በክልሉ የምርታመነትን መጠን አሳድጎ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የዘርፉ ተመራማሪዎች ድርሻ የላቀ ነው ብለዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፀጋዬ ተፈራ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ ተቋሙ የአንድ አመት ዕድሜ ብቻ ያስቆጠረ ቢሆንም የሰብል ጥራት ማስጠበቅ እና የእንስሳት ዝርያን የማሻሻል ስራ ተሰርቷል።
የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከተቋቋመ ጀምሮ ያከናወናቸውን ተግባራት ከባለድርሻ አካላት ጋር እየገመገመ ነው።
ዘጋቢ፡ ሲሳይ ደበበ
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/