በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ሱማሞ አካባቢ የሚገነባውን አየር ማረፊያ ግንባታን የሚያስጀምር ልዑክ አረካ ከተማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ሱማሞ አካባቢ የሚገነባውን አየር ማረፊያ ግንባታን የሚያስጀምር ልዑክ አረካ ከተማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

ሀዋሳ፡ የካቲት 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታውን የሚያስጀምር ልዑክ አረካ ከተማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው፣ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያም እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከአኑዋር ሰይድ ጠቅላላ ተቋራጭ፣ ሲ አር ቲ አማካሪና ባለሙያዎች እንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአረካ ከተማ አቅራቢያ በሱማሞ ሜዳ ለሚገነባው የአየር ማረፊያ ግንባታ የጨረታ ማስታወቂያ በህዳር ወር ማውጣት ይታወቃል።

ዘጋቢ፡ ድርሻዬ ጋሻው – ከዋካ ጣቢያችን