የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ዳር ለማድረስ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው – አቶ ፈቃዱ ተሰማ በሚንስትር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ

የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ዳር ለማድረስ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው – አቶ ፈቃዱ ተሰማ በሚንስትር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ

ሀዋሳ፡ የካቲት 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ዳር ለማድረስ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባልና በሚንስትር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ አስታወቁ።

የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ህዝባዊ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባልና በሚንስትር ማዕረግ የፓርቲው አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፈቃዱ ተሰማ፥ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባልና በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ት/ት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴን፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የት/ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ እንዲሁም የዞንና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ታድመዋል፡፡

በዚህ ወቅት አቶ ፈቃዱ ተሰማ እንዳሉት በማህበረሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎች የህዝቡን የመልማት ፍላጎት ፍንትው አድርገው ያሳዩ በመሆናቸው መንግስት ጥያቄዎችን እየፈታ ነው።

በፌደራል መንግስት እየተሰሩ ያሉ የመንገድ ፕሮጀክቶች ክለሳ ተደርጎ ወደ ስራ እየተገባ ነው ብለዋል።

ለዘመናት ጥያቄ ሆኖ የዘለቀው የሆሳዕና አውሮፕላን ማረፊያ ስራ በቅርቡ ወደ ትግበራ ይገባል ብለዋል።

የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ ስራ ፈጣሪ ትውልድ መፍጠር የሀገር እምቅ አቅምን መጠቀምና ቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ማዘመን አማራጭ የሌለው ተግባር መሆኑን ደግሞ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ በምላሻቸው አመላክተዋል።

የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ ከማዳበሪያ አቅርቦት ጋር ተያይዞ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ በተያዘው ዓመት 1 ነጥብ 6 ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ክልሉ ስለሚገባ የአቅርቦት ችግር አይኖርም ብለዋል።

የትምህርት ቤት ምገባ ስርዓቱም በህብረተሰብ ተሳትፎ ውጤት እየታየ መምጣቱን አመላክተዋል።

ዘጋቢ፡ ባዬ በልስቲ