ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
ይህ የተገለጸው ሀገር አቀፍ ሕዝባዊ ኮንፈረንስ በወላይታ ሶዶ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው።
በከተማው ለኢንቨስትመንት የተወሰደ መሬት ወደ ስራ አለማስገባት ፣ የኑሮ ውድነት መኖር፣ የመሬት ወረራ የመስተዋል የአየር ማረፊያ ግንባታ በወቅቱ አለመጠናቀቅ የከተማዋ ነዋሪዎች ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል ናቸው ።
የስራ አጥ ወጣቶችን ቁጥር በከተማ መቀነስ እንደሚገባ የተመላከተ ሲሆን የትምህርት ስብራት በአግባቡ መጠገንና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ማረጋገጥ ይገባል የሚሉ ዋና ዋና ጥያቄዎች የመድረኩ ተሳታፊዎች አንስተዋል።
ለተነሱ ጥያቄዎች የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል ዶ/ር አብዱ ሁሴን፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ዋና ተጠሪ ገብረመስቀል ጫላ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ 9.5 ሚሊዮን ቋሚና ዘላቂ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን በመድረኩ ማጠቃላያ ላይ የሀረር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ያመላከቱ ሲሆን በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን አገራዊ ምክክር መደገፍ ይገባል ብለዋል።
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበተ በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደገ እንደሚገባ በተጨማሪነትም ተናግረዋል።
የአየር ማረፊያ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ወደ ስራ መገባቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በመንግስት ዋና ተጠሪ በገብረመስቀል ጫላ የተገለፀ ሲሆን የኑሮ ውድነትን ለማርገብ የሌማት ቱሩፋት ማጠናከር እንደሚገባ ዋና የመንግስት ተጠሪው አመላክተዋል፡፡
ለኢንቨስትመንት ተሰጥተው ወደ ስራ ያልገቡ የመሬት ይዞታዎችን የማስመለስ ስራ የከተማ አመራር በቁርጥኙነት እንዲያከናውን መመሪያ እንደወረደ ተናግረዋል።
በሶዶ ከተማ የሚስተዋሉ የመሬት ወረራን ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት መከላከል እንደሚገባ ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷል።
ስራ አጥ ወጣቶች ወደ ስራ ለማስገባት መንግሰት እና ፓርቲ በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት ከቻሉ የትምህርት ስብራትን መጠገን ከባድ አይሆንም ነው የተባለው ፡፡
የሰላም እጦት ችግሮችን በንግግር መፍታት ይገባል ያሉት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳደርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል ዶ/ር አብዱ ሁሴን ናቸው፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተደረገው የኢኮኖሚ ሪፎርም በርካታ አውንታዊ ውጤቶችን እያስመዘገበ ስለመሆኑም ዶ/ር አብዱ አስረድተዋል ፡፡
ዘጋቢ:-ፋሲል ሀይሉ
More Stories
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ10ኛ ጊዜ ያስተማራቸውን የሕክምና ዶክተሮችን እና የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።