የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
በምረቃው ስነ ስርዓቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኤልያስ ዓለሙ የዛሬ ተመራቂዎች በትምህርት ጊዜያቸው ያሳዩትን ትጋት በስራቸውም በመድገም ህብረተሰቡን በቅንነት እንዲያገለግሉ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች አንድነትን በማጠናከር ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት የበኩሉን እንዲወጣ በክብር እንግዲነት የተገኙት የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዶ/ር ዝናቡ ወልደ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
ተመራቂዎች በሰጡት አስተያየት በትምህርት ቆይታቸውን በቀሰሙት ዕውቀት ህብረተሰቡን በታማኝነት እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ፣ በ2ኛና 3ኛ ዲግሪ 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ዘጋቢ፦ ውብሸት ኃ/ማርያም ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በሀገር በቀል ዕውቀት የሚታወቀውን የአካባቢውን እምቅ አቅም አጉልቶ በማሳየት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ዕድገት ማፋጠን እንደሚገባ ተገለፀ
በሩብ ዓመቱ ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለመጀመሪያ ዙር ያሰለጠናቸውን ምልምሎች እያስመረቀ ነው