ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ኮንፍረንስ በዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ሀዋሳ፣የካቲት 15/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ‹‹ከቃል እስከ ባህል›› በሚል መሪ ቃል 2ኛ የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ በተወሰኑ ውሳኔዎችና በተቀመጡ አቅጣጫዎች የተዘጋጀ ከተማ አቀፍ የህዝብ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል
መድረኩን የሚመሩት የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ታዝር ገብረእግዚአብሔር ፣ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሸገር ከተማ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
በመድረኩ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ ዝናቡ ወልዴ ክቡር ( ዶ/ር) የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ እና ሌሎች ከህዝቡ የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
በውይይቱ መድረኩ ከቀረቡ አጀንዳዎች መነሻነት ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የሚነሱ ጥያቄዎች የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚና የፓርቲው ምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ይሰጡበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ:- ውብሸት ከሣሁን ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት