ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ኮንፈረንስ በወላይታ ሶዶ ከተማ መካሄድ ጀመረ፡፡
ሀዋሳ፣ የካቲት 15/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ኮንፈረንስ በወላይታ ሶዶ ከተማ መካሄድ ጀመረ
በኮንፈረንሱን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳደርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል ዶ/ር አብዱ ሁሴን፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክርቤት አባልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ ገብረመስቀል ጫላን ጨምሮ ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ የክልልና የዞን የከተማው አመራሮች፣የአገር ሽማግሌዎች ፣የሀይማኖት አባቶች፣ወጣቶች በተገኙበት ነው ህዝባዊ ውይይት በመካሄድ ላይ የሚገኘው ።
በቀጣይ የውይይቱ መድረኩ ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የሚነሱ ጥያቄዎች የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚና የፓርቲው ምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሀገር አቀፍ የሕዝብ ኮንፈረንስ ከዛሬ ጀምሮ በ25 የተለያዩ ዋና ዋና ከተሞች እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡
ዘጋቢ:- ፋሲል ሀይሉ
More Stories
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት