ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለፀ
መምሪያው ለሴክተሩ ሠራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ባለሙያው ተቋሙ የተቋቋመለትን ዓላማ አውቆ ለማህበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ያሬድ በማብራራት፤ ሠራተኛው የዓመቱን ዕቅድ በማዘጋጀት በወርና በቀናት በመሸንሸን ተግባሩን እንዲያከናውን ታስቦ የተሰጠ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አክለውም መምሪያው ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው የተገኙ የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት የተቋማት ግንባታና የሪፎርም ስራዎች ቡድን መሪ አቶ መኮንን ጪጩ፤ በዞን ደረጃ ያሉት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየት የክህሎት ክፍተት የሚሞላ ስልጠና በዕቅድ በመስጠት ክትትልና ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ባለሙያው ተግባሩን በዕቅድ ዝግጅት ማከናውን ይችል ዘንድ ከክልልና ከዞን ፐብሊክ ሰርቪስ ባገኙት ስልጠና መሰረት ሰነድ በማዘጋጀት ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠታቸውን በመምሪያው የልማት ዕቅድ በጀት ክትትል ግምገማ ግብረመልስ ቡድን መሪ አቶ ክብሩይስፋ ወጋየሁ በመናገር ሠራተኛውም ባገኘው ግንዛቤ ለተገልጋዩ እርካታ መስራት አለበት ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/