የኢፌዴሪ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የተሰሩ ስራዎችን ለመመልከት በክልሉ ተገኝቷል

የኢፌዴሪ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የተሰሩ ስራዎችን ለመመልከት በክልሉ ተገኝቷል

በሚኒስቴሩ የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት በዚህ ወቅት እንዳብራሩት፤ የኮሪደር ልማት ስራ፣ የከተማ አገልግሎት እና ገቢ አሰባሰብ፣ ሴፍትኔት ፕሮግራም እየተመራ ያለበት መንገድ፣ መኖሪያ ቤትና አስተዳደር፣ የመንገድ መሰረተ ልማት ዘርፎች ትኩረት ከሚደረግባቸው ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተሠሩ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ለማየት በሚኒስቴር ዴኤታ የተመራ ቡድን በመምጣቱ መደሰታቸውን የገለፁት  በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ ከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል ልዑኩ በቆይታው በቡታጀራ ወልቂጤና ሆሳዕና የተሠሩ ስራዎችን ይመለከታል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማት  ኮንስትራክሽን ቢሮ ባለፉት ጊዜያት በክልሉ የተሰሩ ስራዎችን ቀርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡

እንደሃገር የተቀመጡ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር አንፃር አበረታች ነው ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው በስራዎች ላይ የታየው የህብረተሰብ ተሳትፎ ጠንካራ መሆኑን አንስተዋል።

በማህበረሰብ ተሳትፎ ብቻ የአስፓልት መንገድ መገንባት መቻሉ ለሌሎች አካባቢዎችም ተሞክሮ የሚሆኑ ነው ያሉት ሃላፊው የህብረተሰቡ ጥያቄ ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ገቢን ማሳደግ ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

ከተረጂነት መላቀቅ እንዲቻል እየተሰራ ያለውም ስራ የሚደነቅ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል።

የገቢ ዕቅድን በዚህ ዓመት መቶ ፐርሰንት አሳድገናል ያሉት በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ ከተማ ልማትና ኢንደስትሪ ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል በአገልግሎት ዘርፉ የህብረተሰቡ እሮሮ ቢቀንስም ሙሉ በሙሉ ዕርካታ ተፈጥሯል ማለት አይቻልም ብለዋል፤ በቀጣይ ዘርፉን ለማሻሻል ይሰራል ነው ያሉት፡፡

ዘጋቢ: ሲሳይ ደበበ