የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አርባምንጭ ከተማ ገቡ።
ሀዋሳ፣ የካቲት 14/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራው ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አርባምንጭ ከተማ ገቡ።
ልኡካን ቡድኑ አርባምንጭ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የጋሞ ዞንና የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንድሁም የጋሞ ሀገር ሽማግሌዎችና የኪነት ቡድን አባላት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ልዑኩ በዛሬው ዕለት በአርባምንጭ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፤ ፀሐይ ጎበና ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ