የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የፖሊዮ (የልጅነት ልምሻ) በሽታ መከላከያ ክትባት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በቀቤና ልዩ ወረዳ ፍቃዶ ጤና ኬላ አስጀመረ
ለአራት ቀናት የሚቆየው የክትባት ዘመቻ በሁሉም የክልሉ ዞኖች ልዩ ወረዳዎች የከተማና የወረዳ አስተዳደሮች እድሚያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ከአንድ ሚሊየን 48 ሺህ በላይ ህጻናት እንደሚከተቡ ተመላክቷል።
የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣና በዋናነት የህፃናትን ጤና በመጉዳት እስከሞት የሚያደርስ ሲሆን ክትባቱን በተገቢው መንገድ በመውሰድ በሽታውን መከላከል ይቻላል ተብሏል።
ክትባቱ በዘመቻ መልክ ቤት ለቤት በሚደረግ ጉብኝት የሚከናወን ሲሆን ሕፃናቱ ከአሁን በፊት ክትባቱን ቢከተቡም ባይከተቡም አሁን የሚሰጠውን የፖሊዮ ክትባት መውሰድ እንደሚኖርባቸው ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ አስቻለው አማረ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ