አርሶ አደሮቹ የተለያዩ የውሃ አማራጮችን በመጠቀምና በቴክኖሎጅ በመታገዝ የተሻለ ምርታማ እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑን የአመያ ዙሪያ ወረዳ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡
አርሶ አደር ደዋና ደርጫና ብዙነሽ በየነ የበጋ ስንዴ በመስኖ በኩታ ገጠም ያመረቱ አርሶ አደሮች ሲሆኑ የግብርና ቴክኖሎጂን በባለሙያ ዕገዛ በመተግበር ማምረታቸውን ተናግረዋል።
ማሳቸውን በሚገባ በማዘጋጀትና የመስኖ ውሃን በአግባቡ በመጠቀም እንዲሁም የተለየ እንክብካቤ በማድረግ የተሻለ ምርት ለማግኘት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
የዘንድሮ የአየር ፀባይ ለበጋ የስንዴ ማሳ ምቹ በመሆኑ ከሄክታር እስከ 35 ኩንታል ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት የበጋ ወቅት የእርሻ ጊዜያቸውን ባለመጠቀማቸው የሚቆጩት አምራቾቹ ዘንድሮ በተፈጠረላቸው ግንዛቤ ወደ ማምረት በመግባታቸው በትንሽ መሬት የተሻለ ምርት በማምረት ከፍተኛ ገንዘብ እያገኙ መሆናቸውን አክለዋል።
የወረዳው ግብርና፣ አካባብ ጥበቃና ህብረት ሥራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን ዳዕሞ ባለፉት አመታት መደበኛና የበጋ መስኖ ያልተለመደና የማይታወቅ ቢሆንም በዚህ ጥቂት አመታት በስንዴ ልማት የተሻለ ምርት ከማግኘት ባለፈ ተግባሩም እየሰፋ መሆኑን ተናግረው በጓሮ አትክልት የመደበኛ መስኖ ሥራ ውጤት ከመመዝገቡ ያለፈ አርሶ አደሩ ሀብት እያፈራ መሆኑን አክለዋል።
አዘጋጅ አብዮት እሸቱ ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ
ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለፀ
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግና ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሀገሪቱ ሰላምን ማስፈን እንደሚገባ ተገለፀ