የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ጋርሾ እና የኮሬ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ ዘመቻውን በኬሌ ከተማ በይፋ አስጀምረዋል።
በዞኑ ከ36 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ህጻናት የፖሊዮ ክትባት ለማድረስ ታቅዶ ለሁለት ተከታታይ ወራት ሲሰራ መቆየቱን የተናገሩት የኮሬ ዞን ጤና ዩኒት ኃላፊ አቶ ደመላሽ ሽፈራው፤ በቂ ዝግጅት በመደረጉ የተሸለ ውጤት እንጠብቃለን ብለዋል።
የኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ በኩላቸው፤ ከአምስት ዓመት በታች ላሉ ህጻናት እየተሰጠ ላለው የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የዞኑ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለው ክትባቱ በትኩረት መሠጠት እንዳለበት አመላክተዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብር የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ጋርሾ በበኩላቸው፤ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ዓላማው ከሀገራችን ፖሊዮን ማጥፋት መሆኑን ተናግረው በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች እየተሠጠ መሆኑን ገልጸዋል።
አንድም ህጻን ሳይከተብ መቅረት የለበትም ያሉት ምክትል ቢሮ ኃላፊው ለዚህም ነው ዘመቻው ቤት ለቤት እንየተደረገ ያለው ብለዋል።
ከፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ጎን ለጎን የህጻናት የምግብ እጥረት፣ የነፍሰ ጡር እናቶች፣ የቆልማማ እግር እና ፖሊዮ የተገኘባቸውም ካሉ የመለየት ስራ የሚሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ሌሎች የዞኑና የኬሌ ከተማ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ዘመቻው ከ14/06/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
ዘጋቢ: እስራኤል ቅጣው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ