በልማቱ ዘርፍ የመጣው ለውጥ ቀጣይነት እንዲኖረው አንድነትን በማጠናከር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር አሳሰበ

በልማቱ ዘርፍ የመጣው ለውጥ ቀጣይነት እንዲኖረው አንድነትን በማጠናከር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር አሳሰበ

የዞኑ አመራሮች በልማትና መልካም አሰተዳደር ጉዳዮችና በቀጣይ አቅጣጫ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በይርጋጨፌ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዶ/ር ዝናቡ ወልደ እንደገለፁት፤ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለፉት ጊዜያት በተደረጉ ጥረቶች በግብርናው፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በከተማ ልማትና በሌሎች ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል፡፡

የዞኑን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ ሁሉንም የገቢ አማራጮች አሟጦ መሠብሰብ ላይ ትኩረት ማድረግ የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ የአመራሩ ቁርጠኝነት፣ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት መጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተደረጉ ጥረቶች በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ያብራሩት አስተዳዳሪው ፤ ይህም ቀጣይነት እንዲኖረው የአመራር ቁርጠኝነት፣ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የጌዴኦ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አበባዬሁ ኢሳያስ በበኩላቸው፤ በአጠቃላይ በዞኑ በተከናወኑት የልማትና የፓርቲ ስራዎች የመጡ ውጤቶችንና ተግዳሮቶችን በመለየት በቀጣይ እንደሀገር የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመከተል በተለያዩ ዘርፎች ያሉትን ችግሮችን ለመፍታት በጋራ ተግባቦትን በመፍጠር መሰራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን