የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ደረጃ በደረጃ በመፍታት የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በማጎልበት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን ለማከናወን ጥረት እየተደረገ መሆኑን በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ ዙር 12ኛ አመት 44 መደበኛ ጉባኤ ተካሂዷል::
በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ፈሰሰወርቅ ገብረሰንበት እንደተናገሩት፤ ምክር ቤቱ የህዝብ ውክልናን በማረጋገጥ ህግ በማውጣት የአስፈጻሚውን ተግባር እየመረመረ የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ይሰራል::
ክትትልና ድጋፉን በማጠናከር የከተማውን ልማትና መልካም አስተዳደር ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል::
በጉባዔው የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር የ2017 በጀት አመት የባለፈው ግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ደረጃ በደረጃ በመፍታት የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በማጎልበት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎች ለማከናወን ጥረት እየተረገ ይገኛል::
የግብር ከፋዩን ግንዛቤ በማሳደግ ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤቶች 480 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 321 ሚሊዮን 440 ሺ ብር በላይ መሰብሰቡን ገልፀዋል::
በኮሪደር ልማት 11.2 ኪሎ ሜትር ዲዛይን ተዘጋጅቶ የወሰን ማስከበር ስራ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ሳምንት ሙሉ ለሙሉ ወደተግባር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ለኢንቨስትመንት 15 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን የገለጹት አቶ ሙራድ ባግባቡ በማያለሙ ላይ እርምጃ በመውሰድና የተሻሉትን በማበረታታት ዘርፉን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል::
በፌደራል መንግስት የሚገነባዉ ከቤተ መንግስት – ሰባት ቤት ማዞሪያ የአስፓልት መንገድ ግንባታ በቅርብ ቀናት እንደሚጀመር አስረድተዋል፡፡
በአለም ባንክ ድጋፍ የከተማው ኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመሮችና ምሰሶዎች የማሻሻል ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በሶስቱም ክፍለ ከተሞች የሰንበት ገበያዎችን የማጠናከር ስራ መሰራቱን ጠቁመው በዚህም አምራችና ሸማቹን በማገናኘት በተመጣጣኝ ዋጋ ግብይት እየተፈፀመ መሆኑን ገልጸዋል::
ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል በተሰራ ስራ 685 ሺ 713 ብር ወደ መንግሥት ካዝና ገቢ መሆኑን በሪፖርቱ አመላክተው ለጤና ተቋማት ትኩረት በመስጠት አገልግሎቱን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን አቶ ሙራድ ተናግረዋል::
በስራ እድል ፈጠራና ኢንተፕራይዞች ልማት ከ8 ሚሊየን 300 ሺ ብር በላይ የቁጠባና ብድር ተጠቃሚ መደረጉን ተናግረዋል::
ህዝብና መንግሥት በመቀራረብ ህገ ወጥነትን በጋራ መከላከል እንደሚገባ አስረድተዋል::
የመሰረተ ልማትና የቄራ አገልግሎት መሻሻል እንዳለባቸው የምክር ቤቱ አባላት ጠቁመው የውሃ ብክነትንና ፍትሃዊ ስርጭትን ማሻሻል እንደሚገባ አንስተዋል::
የከተማው የመልማት ጥያቄ ምላሽ መስጠትና የገቢ አሰባሰብ ስርአቱን ማጠናከር እንደሚገባ የገለፁት አባላቱ ለተጀመሩ ፕሮጀክቶች ትኩረት ሰጥቶ ማጠናቀቅ ይገባል ብለዋል::
የከተማውን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር ህግን ማስከበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል::
በጉባኤው ያለፈው የምክር ቤቱ የአስፈጻሚው እና የፍርድ ቤት የ2017 በጀት አመት የግማሽ በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርበው ውይይት ተደርጓል::
ዘጋቢ፡ ሄኖክ ተክሌ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ
ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለፀ
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግና ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሀገሪቱ ሰላምን ማስፈን እንደሚገባ ተገለፀ