በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተሠሩ ተግባራት ውጤት ማምጣታቸው ተገለጸ
ሀዋሳ፡ የካቲት 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተሰሩ የመኸር ወቅት ተግባራት ውጤታማ እንደነበር የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በክልሉ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ለሀገር ኢኮኖሚ ጉልህ አበርክቶ ያላቸው የመኸር ወቅት ተግባራት በታያዘላቸው እቅድ መሠረት ውጤት ማምጣታቸው ተጠቁሟል፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ የመጣውን ገበያ ማረጋጋትና አስተማማኝ የግብርና ምርት አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ፥ በተሰሩ የመኸር ወቅት የተለያዩ ሰብሎች ውጤት ማምጣት መቻሉን ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) በሪፖርታቸው አመልክታዋል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት 564 ሺህ 194 ሄ/ር መሬት ለማልማት ታቅዶ በቋሚ ሰብል 66ሺህ 909 ሄ/ር፣ በዓመታዊሰብል 483 ሺህ 265 ሄ/ር፣ በባለሀብት እርሻ 7 ሺህ 067 ሄ/ር በድምሩ 557ሺህ 238 ሄ/ር መሬት ማልማት መቻሉ ተመልክቷል።
የመኸር በሁለም ሰብሎች 49 ሚሊዮን 755 ሺህ 302 ኩንታል ምርት ለማምረት በእቅድ የተያዘ ቢሆንም፥ 44 ሚሊዮን 925 ሺህ 619 ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመው፥ በበልግ ወቅት በአዝርዕትና አትክልት ሰብሎች 392 ሺህ 907 ሄ/ር ማሳ ላይ 49 ሚሊዮን 955ሺህ 208 ኩንታል ለማምረት ታቅዶ በዘር ከተሸፈነው 404ሺህ 154 ሄ/ር ማሳ52 ሚሊዮን 736ሺህ 462 ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ
More Stories
የስራ ስር ሰብሎች የግብርና ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተጠቆመ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀመሯል
በመስኖ ሥራ የተሰማሩ የኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች የተለያዩ ሰብሎችን በጥራትና በብዛት በማምረት የተሻለ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡