የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

ሀዋሳ: የካቲት 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6ኛ ዙር 4ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከየካቲት 12 -13/2017 ዓ.ም ድረስ በወልቂጤ ከተማ ያካሒዳል።

ምክር ቤቱ የባለፈውን 6ኛ ዙር 4ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ረቂቅ ቃለጉባኤ መርምሮ በማጽደቅ የሚጀምር ሲሆን፥ የክልሉን መስተዳድር ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን የ2017 በጀት አመት የ6 ወራት አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ በሚኖረው ቆይታ በሌሎች ተጨማሪ አጀንዳዎች ዙሪያ መክሮ ውሳኔዎችን ያሳልፋል።

ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ