አርሶ አደሩ የተሻለ የገቢ ምንጭ እንደሚኖረዉና የኢኮኖሚ አቅሙ የዳበረ እንዲሆን የበጋ መስኖ እርሻ ምርት ትልቅ ዉጤት እያስገኘ እንደሚገኝ የደቡብ አሪ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ
ከዚህ ቀደም የወረዳዉ ግብርና ጽ/ቤት የእርሻ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጋናክሽ አርዳክ፤ በአርሶ አደሩ ዘንድ የበጋ መስኖ ስራ ያልተለመደ በመሆኑ የገቢ አቅማቸዉ ዝቅተኛ እንደነበር አስታዉሰዉ በአሁኑ ሰዓት የግብርና ባለሙያዉን ምክር ተከትሎ ወደ ተግባር እየገባ በመሆኑ በበጋዉ እርሻ የተሻለ ምርት እያገኘ ይገኛል ብለዋል፡፡
በበጋዉ መስኖ እርሻ የጓሮ አትክልት ምርቶች በስፋት የሚመረቱበት እንደሆነ የጠቆሙት ሀላፊዉ፤ በዘንድሮዉ መስኖ እርሻ 1መቶ 20 ሄክታር በስንዴ ምርት ለመሸፈን ታቅዶ እስከአሁን 80 ሄክታር መሸፈናቸዉንና የተባይና የአረም ቁጥጥር እንዲሁም የኬሚካል ርጭት ማከናወናቸዉን አስረድተዋል፡፡
ይህ የበጋ መስኖ እርሻ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሻለ ዉጤት እየታየበት ያለ ተግባር በመሆኑ በቀጣይም አርሶ አደሩ ዘንድ አመርቂ ዉጤት ለማግኘት አስፈላጊዉን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉም ሀላፊዉ ገልጸዋል፡፡
አርሶ አደሮች በበጋዉ መስኖ እርሻ ስራ እያገኙ ባለዉ ምርት ዉጤታማ መሆናቸዉንና ከዚህ ቀደም ከነበራቸዉ የኑሮ ሁኔታ ለውጥ እያገኙ በመምጣታቸው ደስተኛ እንዳደረጋቸውና ስራቸዉንም ይበልጥ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ሰላምነሽ ፍቅሬ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/