የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል በማዘጋጀት አጉልቶ ማሳየትና ማስተዋወቅ ለሁለንተናዊ ለውጥ ወሳኝ መሆኑን የውድድር ተሳትፎና ሥነ ሥርዓት ሰብሳቢ ገለጹ።
እያደገና እየጎለበተ የመጣው የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል ውድድር ሠላምና የህዝቦችን መስተጋብር በማጠናከር ለኢኮኖሚው መነቃቃት አይነተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን የከፋ ዞን ተሳታፊ ወ/ሮ ገልላ ሃ/ማሪያም እና የሸካ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ተወካይ አቶ ብርሃኑ አሾ ተናግረዋል።
የአንድን ህብረተሰብ ባህል አውጥቶ የማሳየቱን እድል የፈጠረና የቱሪዝም ኢኮኖም እያሳደገ ነውም ተብሏል።
በየአካባቢው ተሳታፊዎች ተንቀሳቅሰው ቆይታ ስለሚያደርጉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አገልግሎት በመጠቀም የአካባቢውን ገቢ ያሳድጋልም ብለዋል።
የወንድማማችነት ፍቅርና አንድነትን ያጠናከረ ሠላም እንዲበለጽግ እድል የፈጠረ መሆኑን የኮንታ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መመምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ ደምሴ ተናግረዋል።
ይህንን ጠቃሚ እሴቶች አጠናክሮ ለመቀጠል ባህላዊ እሴቶችን በማጎልበት እየሠሩ እንደሆነና የእንግዶችን ቆይታ ጊዜ ምቹ በማድረግ የአካባቢውን ገጽታ እንደሚገነቡ አክለዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በክልል ደረጃ እየተካሄደ ያለው የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል የህዝቦችን ትስስር ያጠናከረና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ከፍ ያደረገ መሆኑን የክልሉ የስፖርት ተሳትፎና ውድድር ዳይሬክቶሬት የውድድር ተሳትፎና ሥነ ሥርዓት ሰብሳቢ አቶ በየነ ተጋ አብራርተዋል።
እነዚህን ጠቃሚ ባህሎችን በማጎልበትና በማስተዋወቅ ሰላምና አንድነትን በማሳደግ የህዝቦችን ትስስርና አንድነት ማሳደግ እየተቻለ መሆኑንም ተናግረዋል።
ስለሆነም በዩንስኮ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ ነውም ብለዋል።
ዘጋቢ፡ አብዮት እሸቱ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ
ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለፀ
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግና ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሀገሪቱ ሰላምን ማስፈን እንደሚገባ ተገለፀ