በጉባዔው የተወሰኑ ውሳኔዎችና የተቀመጡ አቅጣጫዎች እውን እንዲሆኑ የሚያስችል የፈፃሚ ማዘጋጃ መድረክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሙዱላ ከተማ ተካሂዷል።
ውይይቱን ያስጀመሩት የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ቢኒያም ታደሰ እንደገለጹት፤ የብልጽግና ፓርቲ በየደረጃው የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ዓይነተኛ ለውጥ እየተመዘገበ ይገኛል።
በዚህም የሙዱላ ከተማ “የከተማ አስተዳደር” መዋቅር ካገኘች ወዲህ በለውጥ ሂደት ላይ መሆኗን እየተገነቡ የሚገኙ የመሰረተ ልማት አውታሮች ማሳያ እንደሆኑም ገልፀዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪውንና የንግዱን ማህበረሰብ እንዲሁም በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የሚገኙ የጠምባሮ ብሄረሰብ አባላትንና ወዳጆችን በማስተባበር በሁለተኛው የብልጽግና መደበኛ ጉባዔ የተወሰኑ ውሳኔዎችና የተቀመጡ አቅጣጫዎች ተፈፃሚ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ከንቲባው አመላክተዋል።
በሁለተኛው የብልጽግና ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎችንና የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በህዝብ መድረኩ ገለፃ ያደረጉት የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መኮንን ወጮሬ እንዳሉት ገዢ ትርክቶችን ማስፋትና ከነጠላ ትርክቶች መቆጠብ ይገባል።
አባሉና አመራሩ ለጠንካራ ሀገር ግንባታ እንዲሁም ህብረብሔራዊ አንድነትን በአስተሳሰብና በተግባር በማስተሳሰር ለጉባኤው ውሳኔ ተፈፃሚነት የድርሻውን ሊወጡ እንደሚገባም አቶ መኮንን ገልፀዋል።
የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ሀብታሙ በላይነህ በበኩላቸው፤ የብልጽግና ፓርቲ ለልዩ ወረዳው ከሰላሳ ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ ሳይመለሱ የቆዩ የህዝብ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘታቸውን ገልፀው መሰል የብልጽግና ፓርቲ ትሩፋቶች ያስገኙትን እድሎች በመጠቀም ለላቀ ለውጥ ልንረባረብ ይገባል ብለዋል።
ብልጽግናን በቤተሰብና በግለሰብ ደረጃ ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነትን ይበልጥ ማጎልበት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል።
በልዩ ወረዳው የመንግስት ሰራተኞች የወር ደመወዝ መዘግየት ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ከእዳ ለመውጣት የሚያስችሉ ስልቶችን ወጥኖ መስራት እንደሚሻም እንጂነር ሀብታሙ ተናግረዋል።
በሁለተኛው የብልጽግና ጉባዔ የተወሰኑ ውሳኔዎችና የተቀመጡ አቅጣጫዎች ተፈፃሚ እንዲሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አቶ አቡቶ አኒቶ ገልፀዋል።
የገዢ ትርክቶች መሸርሸር በሀገር ግንባታ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳያሳድር ሁሉም ከነጠላ ትርክት እራሱን በማራቅ ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር የላቀ አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለበትም ዋና አፈ ጉባኤው አሳስበዋል።
ያነጋገርናቸው አንዳንድ የመድረኩ ተሳታፊዎች በሁለተኛው የብልጽግና ጉባዔ የተወሰኑ ውሳኔዎችና የተቀመጡ አቅጣጫዎች ከዳር እንዲደርሱ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልፀው፤ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በማረም ፍትሃዊ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ አመራሩ በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅበትም ጠቁመዋል።
በጉባኤው የተወሰኑ ውሳኔዎችና የተቀመጡ አቅጣጫዎች በሙዱላ ከተማ በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተለይም፤ የሃይማኖት አባቶች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ሲቪክ ማህበራት እንዲሁም የሙዱላ ከተማ አስተዳዳሪና የልዩ ወረዳው አስተባባሪ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።
ዘጋቢ: ጡሚሶ ዳንኤል – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ
ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለፀ
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግና ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሀገሪቱ ሰላምን ማስፈን እንደሚገባ ተገለፀ