ሀዋሳ፡ የካቲት 10/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የተሻለ ተቋማዊ አደረጃጀትን መፍጠር ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የላቀ በመሆኑ በተቀናጀ ርብርብ ሊሠራ እንደሚገባ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ገለጹ፡፡
በክልሉ ታርጫ ማዕከል የሚገኙ የፓርቲ ቤተሰብ አባላት “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሃሳብ መነሻ በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔና በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ተግባራቸውን ለማከናወን ተቀናጅተው እንደሚሠሩም አስረድተዋል።
በውይይታቸውም ከቀረበው ሰነድ መነሻ ለተግባር ውጤታማነት ትኩረት ተሰጥቶ ካልተሠራ የኑሮ ውድነትን መቅረፍ እንደማይቻልም ተገልጿል።
ተቋማዊ አቅም ግንባታ በተደራጀ ሁኔታ በማጠናከር ለጠንካራ ሀገር ግንባታ የድርሻቸውን ለመወጣት በተቀናጀ ርብርብ ተግባራቸውን እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል።
አካታች የሆነው ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ተቋማዊ አንድነትን ከመፍጠር ባለፈ
በክልሉ የተጀመሩ ኢንሼቲቮች ውጤታማ እንዲሆኑ በትኩረት መሥራት ተገቢ እንደሆነም ገልጸዋል።
አሁን ላይ በክልሉ የሚገኙ አመራሮች የፖለቲካ ተግባቦት ሥራ በተጠናከረ አኳኋን እያከናወኑ እንደሚገኙም ተገልጿል።
በማዕድን፣ በቡና፣ በቱሪዝምና በሌሎች የገቢ ማስገኛ ምንጮች ላይ በትኩረት በመሥራት ዜጎችን በየደረጃው ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ውጤት እንዲመዘገብ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ነው የገለጹት።
ዘጋቢ፡ መሣይ መሠለ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ
ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለፀ
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግና ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሀገሪቱ ሰላምን ማስፈን እንደሚገባ ተገለፀ