በበጀት አመቱ 132.8 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ ተይዟል – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
ሀዋሳ፡ የካቲት 07/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በበጀት አመቱ 132.8 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ መያዙን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለፁ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ለምክር ቤቱ የክልሉን መንግሥት የስድስት ወራት አፈፃፀም ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት፤ በግማሽ አመቱ በተደረገው እንቅስቃሴ 132.8ሚሊዮን ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ ዕቃ የተያዘ ሲሆን በዚህ ተግባር የተሳፉ 64 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተደረገ ጥናት 870 የትምህርት ማስረጃዎች ሀሰተኛ ሆነው የተገኙ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 862ቱ ላይ የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።
ህገ-ወጥ ቅጥርና ዝውውር እንዲሁም ዕድገት የእርምት እርምጃ መወሰዱን የተጠቀሰ ሲሆን በህገ-ወጥ ተግባሩ ላይ የተሳተፉ 23 አመራሮችን የማባረር፣ 21 አመራሮች ላይ የማስጠንቀቂያ እንዲሁም 179 ላይ ደግሞ አስተዳዳራዊ እርምጃዎች ተወስዶባቸዋል።
በዚህም ህገ ወጥ ተግባር መንግሥት ሊያጣ የነበረውን 72.6 ሚሊዮን ብር ማዳን የተቻለ መሆኑን በመግለጽ ህገ-ወጦችን የማጥራት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ፣ የአደንዛዥ ዕፅ፣ የሰዎችና የንግድ ምርት ዝውውርን ለመከላከል በተከናወነ ተግባር 89 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች፣ 4ሺህ 469 ተተኳሽ ጥይቶች እንዲሁም 61 ካርታ ሲያዘዋዉሩ ከነበሩ 80 ህገ-ወጥ ግለሰቦች ጋር በቁጥጥር ስር በማዋል በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ መከናወኑን በሪፖርቱ ጠቅሰዋል።
209 የትራፊክ አደጋ ባለፉት 6 ወራት መመዝገቡን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም የ138 ሰው ህይወት መጥፋቱንና 14 ሚሊየን 859ሺህ 120 ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ
More Stories
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት