የምክር ቤት አባላት ለህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በጋራ ሊሰሩ ይገባል – ዋና አፈ ጉባዔ ፀሀይ ወራሳ
ሀዋሳ፡ የካቲት 07/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የምክር ቤት አባላት ለህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ፀሀይ ወራሳ ገለጹ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፀሀይ ወራሳ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ በለውጥ ሂደት ወቅት የገጠሟትን ፈተናዎች በጥበብ እያለፈች ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ዘርፎች ስኬቶች እየተመዘገቡ ስለመሆኑ የጠቀሱት ወይዘሮ ፀሀይ፤ ስኬቱም የጠንካራ ፓርቲ እና መንግሥት ውጤት ነው በማለት ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ልዩነትን በአንድነት ውስጥ ውበት አድርጎ እየተጓዘ ያለ ሲሆን ክልሉ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ የራሱን አሻራ እያሳረፈ ነውም ብለዋል።
ነጣጣይ ትርክቶችን ወደጎን በመተው ለሀገር አንድነት በጋራ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የምክር ቤት አባላት በጋራ መስራት እንዳለባቸው አመልክተዋል።
በበጀት አመቱ መጀመሪያ ላይ ፈፃሚ አካላት የዕቅድ ውል አስረው ወደ ስራ እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን ምክር ቤቱ በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል የቅርብ ክትትል መደረጉንም አፈ ጉባኤዋ አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ
More Stories
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት