ወጣቶች የቡርጂ ዘመን መለወጫ “ዎናንካ አያና” በዓል በድምቀት ለማክበር በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ እየተሰተፉ ነው
ሀዋሳ፡ የካቲት 07/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ወጣቶች የቡርጂ ዘመን መለወጫ “ዎናንካ አያና” በዓል በድምቀት ለማክበር በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን የቡርጂ ዞንና ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ገለፀ።
አስተያየታቸውን የሰጡን ወጣቶች “ዎናንካ አያና” የዘመን መለወጫ በዓል የማንነታችን መገለጫ በመሆኑ ከገቢ ማሰባሰብ እስከ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ቅድመ ዝግጅት ተግባራት ላይ መሰማራታቸውን ተናግረዋል።
አቶ በየነ አሊ የቡርጂ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት ዩኒት አስተባባሪ በበኩላቸው፥ ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ የሚከበረው የ”ወናንካ አያና” ዘመን መለወጫ በዓል በድምቀት እንዲከበር የገቢ ማሰባሰብ፣ አከባቢ የማፅዳት እና ማስዋብ፣ የማስተዋወቅ፣ የሰላም እና የፀጥታ እና የስፖርት ውድድር ቅድመ ዝግጅት በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ወጣቶቹ የዘመን መለወጫ ወናንካ በዓል ባህሉ እና ማንነቱ የሚንፀባረቅበት ዕለት በመሆኑ ለበዓሉ ድምቀት የሚሆኑ የስፖርት ውድድሮችን እያዘጋጁ የቆዩ ሲሆን፥ የዘንድሮ የወናንካ የዘመን መለወጫ በዓል ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልኩ የጎዳና ላይ የእርምጃ ውድድር አስቀድሞ በየካቲት 08 እንዲደረግ ቅድመ-ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
አስታየታቸውን ከሰጡን የዝግጅቱ ተሳታፊ ወጣቶች መካከል ወጣት ቻለው ሳሙኤል እና አህመድ መሐመድ የወናንካ የዘመን መለወጫ በዓል በድምቀት እንዲከበር የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ለስኬታማነቱ ገቢ የማሰባሰብ፣ በአከባቢ ማጽዳት እና ከተማን የማስዋብ፣ እንዲሁም የፀጥታ እና ሠላም ጉዳዮች ዙሪያ በንቃት እየተሳተፉ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ ከበዓሉ ዕለት ሁለት ቀን አስቀድሞ የጎዳና ላይ ውድድር ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አውስተው በውድድሩ በሁሉም የዕድሜ ደረጃ ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለሚሳተፉ ስፖርታዊ ጨዋነትን በጠበቀ መልኩ እንዲካሄድ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ አስረድተዋል።
ከዋዜማው ጀምሮ በዓሉ ፍፃሜ እንግዶችን ተቀብሎ በማስተናገድ፣ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በሠላም እንዲከበር የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ወጣቶችን በማንቃት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዘጋቢ: አብዶ አያላ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት