በክልሉ ያሉ የመስኖ ተቋማት ትክክለኛ መረጃዎችን በመሰብሰብ የመስኖ ልማት ስራ እንዲካሄድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
ሀዋሳ፡ የካቲት 06/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ ያሉ የመስኖ ተቋማት ትክክለኛ መረጃዎችን በመሰብሰብ የመስኖ ልማት ስራ እንዲካሄድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር መሀመድ ሲራጅ ጥሪ አቀረቡ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት የመስኖ ተቋማት ኢንቨንተሪ መረጃ አሰባሰብ ላይ ለዞንና ልዩ ወረዳዎች ስልጠና እየሰጠ ነው።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር መሀመድ ሲራጅ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት የመስኖ ተቋማት መረጃ አሰባሰብ በየጊዜው ወቅታዊና ዘመናዊ መደረግ እንዳለባቸው ገልፀዋል ።
በክልሉ የሚገኙ የአስተዳደር መዋቅሮች በእቅዳቸው መሰረት እየሰሩ የቆዩ ቢሆንም በሚፈለገው ልክ መረጃዎች በዘመናዊ መልኩ እየተሰበሰበ አለመሆኑን አመላክተዋል።
በዚህም እስከ አሁን የመጣንበትን ሂደት በሚክስ መልኩ ተቋማት መረጃዎችን መሰብሰብ እንዳለባቸው ውሳኔ ላይ ተደርሷል ያሉት ኢንጂነር መሀመድ፥ እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖ ተቋማት መረጃ አሰባሰብ ስራ በ2014 ዓ.ም መከናወኑን ጠቁመዋል፡፡
በዞንና ልዩ ወረዳ መዋቅር ላይ የሚሰበሰቡ መረጃዎች የወጥነት ችግሮች ያለባቸው በመሆኑ በክልሉ ያሉ መረጃዎችን ወጥ ለማድረግ እና በአዲስ መልክ በተደራጀው ክልል መረጃዎችን በአዲስ መልኩ መሰብሰብ እንዳለበት በመታመኑ ነው የዛሬውን ስልጠና ማዘጋጀት ያስፈለገው ብለዋል።
ስለሆነም ከስልጠናው በኃላ የሚሰበሰበው መረጃ በትክክልና በግልፅ በክልሉ ያሉ የመስኖ ተቋማትን ሀብት የሚገልፅ መሆን መቻል እንዳለበት አሳስበዋል።
ስልጠናው በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ እንደሚሆን አብራርተዋል።
በሁሉም መዋቅሮች በስልጠናው ላይ የተገኙ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙዎች በየአከባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ያሉ የዕውቀትና የክህሎት ክፍቶችን ለመሙላት ትኩረት ሰጥተው ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ትክክለኛ የመስኖ ተቋማት መረጃዎችን በመሰብሰብ የመስኖ ልማት እንዲካሄድ የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርበዋል።
በስልጠናው ላይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖ ቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር መሀመድ ሲራጅን ጨምሮ የዞንና የልዩ ወረዳ የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ ተዘራ በቀለ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት