የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ መነቃቃትን እና ተጨማሪ እድል የፈጠረ ነው – ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ
ሀዋሳ፡ የካቲት 06/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ መነቃቃትን እና ተጨማሪ እድል የፈጠረ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫን አስመልክቶ የተዘጋጀ መድረክ ታርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በክልሉ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸሙ ከዕቅዱ አንጻር የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት ቢሆንም ካለው አቅም አንጻር አሁንም ትኩረትን የሚፈልግ ስለመሆኑ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናግረዋል።
የገቢ አሰባሰብ ሂደትን ዘመናዊ በማድረግ በኤሌክትሮኒክ ታክስና በቴሌ ብር ግብር አሰባሰብ የተሰሩ ተግባራት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተዋል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ በበኩላቸው፤ የክልሉ መንግስት በጀትን 60 በመቶ በውስጥ ገቢ ለመሸፈን በማቀድ ወደ ሥራ መግባቱንና ለዚሁ ተግባራዊነት በክልሉ 64 ታክስ ማዕከላት በማቋቋም ግብር ከፋዩ በኤሌክትሮኒክ ታክስ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
የግብር ስወራ ያልተገባ ገቢ ለማግኘት ሲባል የሚደረግን ህገ-ወጥነትን ለመከላል በቀጣይነት በትኩረት የሚሠሩ ተግባራትን መከወን የሚገባ ነውም ብለዋል።
በምክክር መድረኩ የሁለቱም ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች፣ የክልል አስፈፃሚ አካላት፤ የዞኖች ዋና አስተዳዳሪዎች፤ የወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፡ አዲስዓለም ታዬ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
በካፋ ዞን ጨና ወረዳ በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) የተከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር የልምድ ልውውጥ ተደረገ
ሳታ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ በአርባ ምንጭ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 132 ተማሪዎችን አስመረቀ
በዕቅድ የሚመራ የመፈፀም አቅሙ ያደገ ሲቪል ሰርቫንት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ገለፀ