ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) “ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘ ሃገራዊ የፓናል ውይይትና የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ በቡታጅራ ከተማ አስጀመሩ
ሀዋሳ፡ የካቲት 06/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀውን “ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘ ሃገራዊ የፓናል ውይይትና የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ በቡታጅራ ከተማ አስጀምረዋል፡፡
በፎቶ ግራፍ አውደ ርዕዩ በክልሉ ያለውን የቱሪዝም፣ የኢኮኖሚና የግብርና ሃብቶች እንዲሁም ሃገር በቀል የዕርቀ ሰላም አቅጣጫዎችን የሚጠቁሙ ምስሎች ለዕይታ ቀርበዋል።
ውይይቱ “ሰላምና ኢኮኖሚ ስለ ኢትዮጵያ” በሚል እየተካሄደ ሲሆን ይህ መድረክ በሁለተኛው ምዕራፍ የመጀመሪያው መሆኑም ተጠቁሟል።
በመርሃ-ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር)፣ በኢፌዲሪ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ምህረተአብ እስራኤል
More Stories
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት