በ2ኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የአመራር የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው
ሀዋሳ፡ የካቲት 05/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ”መፍጠን እና መፍጠር ለጉባኤያችን ውሳኔዎች ስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ በጉራጌ ዞን በ2ኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የአመራር የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው።
በሁሉም ዘርፍ ከቃል ወደ ባህል ለመሸጋገር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ይበልጥ በማጠናከር ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል።።
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብሬ ጋጌ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል እና የዞኑ የስራ ኃላፊዎች በመድረኩ ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ሚፍታ ጀማል – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት