ለፓርቲው ውሳኔና ቀጣይ አቅጣጫዎች ተፈፃሚነት አመራሩ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ የካቲት 3/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በብልጽግና ፖርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ለተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ተፈፃሚነት አመራሩና አባላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የአሪ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
“ከቃል እስከ ባህል” በሚል ርዕስ የብልጽግና ፖርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በተወሰኑ ውሳኔዎችና በተቀመጡ አቅጣጫዎች ዙሪያ የኣሪ ዞን አመራሮች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አታ መድረኩ የብልጽግና ፖርቲ በምስረታው ወቅት ለህዝቡ የገባውን ቃል በተግባር ያሳየበትና በሂደቱ ያጋጠማውን ፈተናዎች በጽናት መወጣቱን ጠቁመዋል።
ዋና አስተዳዳሪው አያይዘውም፥ አመራሩ ፓርቲው ላለፉት ጊዜያት የፈፀማቸውንና የቀሪ ጊዜያት ቁልፍ ተግባራትን በሚገባ ተረድቶ በኃላፊነት እንዲወጣ ለማስቻል የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን አመላክተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊና የመድረኩ አስተባባሪ ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ በበኩላቸው፥ መድረኩ የብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው ያስተላለፋቸው ውሳኔዎችና ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ ከአመራርና አባላቱ ጋር መግባባት መፍጠር ነው ብለዋል።
ፓርቲው በህቦች የጋራ ፍላጎት የተመሠረተና በርካታ የአስተሳሰብና አመለካከት ለውጥ የተመዘገበበት እንደሆነም አመላክተዋል።
የብልጽግና ፖርቲ ባለፉት አመታት ከፖለቲካ ሪፎርም ባሻገር በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን አመላክተው፥ በፓርቲው ሁለተኛ ጉባኤ ለተላለፉ ውሳኔዎችና ለተቀመጡ አቅጣጫዎች ተፈፃሚነት አመራሩና አባሉ ከምንም ጊዜ በላይ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
በመድረኩ የዞኑ ሁሉም አመራር፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴዎች የተሳተፉ ሲሆን ውይይቱ እስከ ቀበሌ መዋቅር እንደሚቀጥል ተመላክቷል።
ዘጋቢ፡ መልካሙ ቡርዝዳቦ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት