የሕዝብ ተሳትፎን መሠረት ያደረገ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሥርዓትን ለመዘርጋት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የደምባ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ
“የመሬት ሀብታችን ለዕድገታችን” በሚል መሪ ቃል በጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም፣ በመሬት መረጃ ሥርዓተ-ግንባታ እና በመሬት ግብይት ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።
የደምባ ጎፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንዳርጌ አራታ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት፤ መሬት የዜጎች የምግብ ዋስትና መሠረት በመሆኑ ህጋዊ አሰራርን በመከተል ቀደም ሲል በነበረው ሥርአት አርሶ አደሩ መሬትን በአግባቡ ያለመጠቀም ችግሮችን በፍጥነት በመሻገር አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ባደረገ መልኩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ መሠራት አለበት።
የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘይቤ ለመቀየር ከሰርተፊኬት በኋላ ይፋዊ የመሬት ኪራይ ውል ሥርዓት መተግበርና አርሶ አደሩ በሰርተፊኬቱ ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም እንዲያገኝ በማድረግ በየደረጃው የሚገኙ አመራር አካላት በትኩረ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡
አርሶ አደሩ የመሬት ግብር መክፈል እንደ ዕዳ ሳይቆጥር ሁሉም አርሶ አደር በተሰጣቸው ጊዜ ገደብ ከፍለው መጨረስ እንዳለባቸው አስተዳዳሪው በአፅንኦት አሳስበዋል።
መሬት ከሀብቶች ሁሉ የላቀ ሀብት ነው ያሉት የደምባ ጎፋ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ አላ፤ ቴክኖሎጂን መጠቀም የግብርና ተግባራትን ለማሳለጥ እና ለማሳደግ ብቸኛ አመራጭ እንደሆነ ተናግረው አርሶ አደሮች በእርሻ ልማት ስራ ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው አብራርተዋል።
የእርሻ ስራ ከባህላዊ ወደ ዘመናዊ በመሻገር በመካናይዜሽንና ኩታ ገጠም መሰራት እንዳለበት ተናግረው፤ ለዚህም ትራክተር እና ምርጥ ዘር በበቂ ሁኔታ በማዘጋጀት በሙሉ አቅም ወደ ተግባር መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
ከሰደድ እሳት፣ ከአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራዎች አንጻር የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ ላይ ህዝባዊ ተሳትፎን በማሳደግ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት መስጠት ተገቢ መሆኑን አቶ አድማሱ ተናግረዋል።
ከመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ስርዓት ጋር ተያይዞ መሬት መሸጥና መለወጥ የማይቻል መሆኑን የተናገሩት የደምባ ጎፋ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የመሬት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኡመር ሀሰን፤ በስጦታ፣ በውርስ እና በማደል ወይም ያጋጠሙ ችግሮች ታይተው መሬትን አከራይተው መጠቀም እንደሚቻል እንዲሁም በይዞታው ላይ ያፈራውን ሀብትና ንብረት ሸጦ የመጠቀም መብት እንዳለው አብራርተዋል።
በዘርፉ እስካሁን በተሰራው ሥራ በርካታ ለውጦች በመምጣታቸው ተግባሩን በደስታ እያከናወንን ነው ብለው፤ ከተፋሰስ ልማት ስራው ጎን ለጎን ሌሎች የግብርና ሥራዎችን ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን የመድረኩ ተሳታፊዎች አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ ድጋፌ ድክሬ – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት