የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የፕላን መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተላቸውን ተቋማት ሪፖርት እያደመጠ ነው
ሀዋሳ: ጥር 28/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የፕላን መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተላቸውን ተቋማት የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርት እየገመገመ ነው።
የክልሉ ምክር ቤት የፕላን መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፥ የዘርፉን ተቋማት የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እየገመገመ ነው።
ቋሚ ኮሚቴው በሚከታተላች ተቋማት በ2017 መጀመሪያ ግማሽ አመት የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በቀረበው ሪፖርት ላይ አስተያየት፣ ጥያቄዎችንና ግብረ መልሶችን እየሰጠ ነው።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የፕላን መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እንቁ ዮሐንስ ጨምሮ የቋሚ ኮሚቴ አባላትና የተቋማቱ የቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም የማኔጅመንት አባላት እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ: ስላባት ባህሪው

More Stories
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ
በአጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የመንግስት የልማት ክፍተት በመሙላት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በሌማት ትሩፋት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የምዕራብ አባያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ