የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማትን የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ
ሀዋሳ: ጥር 28/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማትን የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እያካሔደ ነው።
የክልሉ ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴም የክልሉን ጤና ቢሮ እንዲሁም የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል።
በዚህም ቋሚ ኮሚቴው የተቋማቱን የግማሽ ዓመት ሪፖርት በማድመጥ ጥያቄዎችንና ግብረ መልሶችን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በግማሽ ዓመቱ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እመቤት ወንድሙን ጨምሮ የቋሚ ኮሚቴ አባላትና የተቋማቱ የቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም የማናጅመንት አካላት ተሳታፊ እየሆኑ ይገኛሉ።
ዘጋቢ: ቃልአብ ጸጋዬ
More Stories
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የሆሳዕና እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!