የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚያሰለጥኑት የሰው ሃይል ብቁና ችግር ፈቺ እንዲሆን በትኩረት መስራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ አስታወቀ
ቢሮው በስልጠና መሳሪያዎች ደህንነት አጠባበቅ፣ አጠቃቀም እና አስተዳደር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና በምሁር አክሊል ወረዳ ሀዋርያት ከተማ በሚገኘዉ የሀዋርያት ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በመሰጠት ላይ ነው::
ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት የቢሮው ምክትልና የተቋማት አቅም ግንባታና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር ሰለሞን ፈርሻ እንደተናገሩት፤ የስልጠና ጥራትን ለማሳካት የስልጠና መሳሪያዎች ከፍተኛ ግበዓት መሆናቸዉን አንስተዋል::
ኢንጂነር ሰለሞን ፈርሻ አክለዉም ወቅቱ የሚፈለገዉን የቴክኖሎጂ እሳቤዎችን ከመጨበጥ ባለፈ የስልጠና መሳሪያዎች ደህንነትና አጠቃቀም ትኩረት የሚሻቸዉ ጉዳዮች መሆናቸዉን ጠቅሰዋል::
የክህሎት ልማትን ተግባራዊ ለማድረግ ሰልጣኞች በትኩረትና በንቃት እንዲሳተፉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::
የምሁር አክሊል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪና የሀዋርያት ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ብስራት ገብሩ እንደተናገሩት፤ ዛሬና ነገን ታሳቢ ያደረገ ብቃት ያለዉ በራሱ የሚተማመን በእዉቀት የተቃኘና አሻግሮ የሚመለከት ትዉልድ መፍጠር የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሀላፊነት ነዉ ብለዋል::
የሀዋርያት ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን አቶ ትዛዙ ፈቃዱ፤ የኤሌክትሪካል ዲፓርትመንት የአዉቶሞቲቭ የፈርኒቸር የሜታል ወርክ የICT የጋርመንትና የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንቶችን አስጎብኝተዋል፡፡
በክልሉ ከሚገኙ ፖሊ ቴክኒክ፣ ኢንዱስትሪያልና ኮንስትራክሽን ኮሌጆች የተቋማት አቅም ግንባታና ጥራት ቁጥጥር የተውጣጡ የጥገና ቡድን አባላት የስልጠና አሰልጣኞች ተሳታፊዎች መሆናቸውም የተጠቆመ ሲሆን ስልጠናዉም ለተከታታይ 5 ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
ዘጋቢ፡ መሀሪ አብልከሪም – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የሃገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
አርሶ አደሩ በእንሰት ተክል የምግብ ዋስትናውን በማረጋገጥ የኢኮኖሚ አቅሙን እንድያሳድግ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
ህብረት ሥራ ማህበራት ለሀገር ብልፅግና መሪ ተዋናይ ናቸው ሲል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ገለፀ