የመሬት ለምነትን ለማስጠበቅ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ጥር 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የመሬት ለምነትን ለማስጠበቅ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በዳውሮ ዞን የሎማ ቦሣ ወረዳ የግብርና አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
በወረዳው በዘንድሮ የተፋሰስ ልማት ስራ ከ45 በላይ ንዑስ ተፋሰስ እና ከ22 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ እንደሚለማ ተመላክቷል፡፡
“የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም የተፋሰስ ልማት ስራ በዳውሮ ዞን በሎማ ቦሳ ወረዳ ዚማ ዋሩማ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል።
የዳውሮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢዮብ ቶማስ እንደተናገሩት፥ የተፋሰስ ልማት ስራ አፈር በንፋስ እና በዝናብ ተሸርሽሮ እንዳይወሰድ ለመከላከልና የአፈር ለምነት ተጠብቆ እንድቆይ ከማድረግ ረገድ ያለው ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የተፋሰስ ስራ ውጤታማ እንዲሆን በህብረተሰቡ ዘንድ የታየው ተነሳሽነት የሚደነቅ እንደሆነ የገለጹት አቶ ኢዮብ፥ ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለ አካባቢን ለማውረስ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት መወጣት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
የዳውሮ ዞን ግብርና አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የተፈጥሮ ሀብትና አከባቢ ጥበቃ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምትኩ ለይኩን በበኩላቸው፥ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት የተራቆቱ አከባቢዎች መልሰው ለማልት የተፋሰስ ልማት ስራ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።
ባለፉት ዓመታት በወረዳው በተሰራዉ የተፋሰስ ልማት የመሬት ለምነት በመጠበቁ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የተፋሰስ ልማት ስራ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ የሎማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዘለቀ ሲሳይ ገልጸዋል።
ለተከታታይ 30 ቀናት በሚቆየው በዚህ የተፋሰስ ልማት ስራ የአከባቢው ህብረተሰብ በነቂስ ወጥቶ በመሳተፍ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በወረዳው በዘንድሮ የተፋሰስ ልማት ስራ ከ45 በላይ ንዑስ ተፋሰስ ከ22 ሺህ 500 መቶ ሄክታር በላይ መሬት እንደሚለማ የገለፁት በወረዳው የግብርና አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኪዳኔ በቀለ፥ ከ26 ሺህ 613 በላይ የህብረተስ ክፍሎች እንደሚሳተፉም አያይዘው ገልጸዋል ።
ዘጋቢ : አሸናፊ ግዛው – ከዋካ ጣባያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/